ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ ለምርጥ ዘር ልማት 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኙ

የብአዴን 37ኛው የምስረታ በዓል በባህርዳር ለታጋዮች እውቅና በመስጠት ተከብሯል

በአዲስ አበባ የሚጣሉ የፕላስቲክ ውጤቶች የከተማዋን ውበት እያበላሹ ነው

ወጣቶችን በማደራጀትና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ተጠየቀ

በባህርዳር ቢአኤካ በተባለ የግል ድርጅት የተቋቋመው የእምነበረድና ቀለም ፋብሪካ ተመረቀ

ብአዴን ለነባር ታጋዮች በሚሊንየም አዳራሽ የእውቅና ሽልማት ሰጠ

ብአዴን ህዝባዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአማራና ትግራይ ክልል ህዝቦች የጋራ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ ጉብኝት አደረጉ

ብአዴን ለህዝባዊ ወገንተኝነት በፅናት ሊታገል እንደሚገባ ተጠቆመ

ምርጫ ምርጫ

Back

በምርጫው ጊዜያዊ ውጤት ላይ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሰሙት አቤቱታ መሰረት የሌለው እንደሆነ ቦርዱ አስታወቀ

የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ "ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ አልነበረም" በማለት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚያሰሙት አቤቱታ መሰረት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ሀሙስ ግንቦት 27 ፣2007 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሁሉም ፓርቲዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከመክፈቻ ቃለ-ጉባዔ ጀምሮ እስከ መተማመኛ ቅፅ ድረስ ሂደቱን ተቀብለውትና አምነውበት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

በደምፅ አሰጣጥ ሂደቱም አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ለቦርዱ ያቀረበው ቅሬታ አለመኖሩን ነው የገለጸው።

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ቦርዱ ጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ ካደረገ በኋላ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን ችግሮች የነበሩበት አስመስለው የሚያናፍሱት ወሬ ፍጹም ተቀባይነት የለውም።

"ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም አሳታፊ ሆኖ የበርካቶችን አመኔታ አትርፎ እያለ ፣ውጤቱ ከታወቀ በኋላ የሚነሱ መሰረተ ቢስ ምክንያቶች በቦርዱ በኩል ተቀባይነት የላቸውም" ብለዋል።

የምርጫውን አጠቃላይ ሂደትና ዴሞክራሲያዊነት አስመልክቶ ከሩብ ሚሊዮን በላይ የህዝብና የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ጭምር ማረጋገጫ መስጠታቸውን ለማሳያነት አንስተዋል።

በምርጫ ፉክክሩ ከተሳተፉት 58 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥም በርካቶቹ የምርጫውን ሂደትና ጊዜያዊ ውጤቱን በፀጋ መቀበላቸው ፕሮፌሰ መርጋ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እውነታውን ወደ ጎን በመተው የህዝብን ውሳኔ ላለመቀበል ምክንያቶችን ማስቀመጣቸው ተገቢነት የሌለው እንደሆነ ነው የተናገሩት።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚያብሄር በበኩላቸው በመራጮችና በዕጩዎች ምዝገባ ወቅት ቀርበው ከነበሩት ቅሬታዎች ውጭ በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የቀረበ ቅሬታ የለም።

እንደ እርሳቸው ገለፃ በቅድመ ምርጫው ወቅት ቀርበው የነበሩት ወደ 48 የሚደርሱ ቅሬታዎችም ብዙዎቹ እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል።

አምስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ መልኩ ሠላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቀቁንም ገልጸዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ የቀረው የቦንጋ ገዋታ ምርጫም በመጪው ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን ነው ቦርዱ በመግለጫው ያስታወቀው።

ምንጭ፡ ኢዜአ