ቱርክ መፈንቀለ መንግስት ሙከራ የተደረገበትን 1ኛ ዓመት ልታስብ ነው

ሐምሌ 08፣2009

ቱርክ የመፈንቀለ መንግስት ሙከራ የከሸፈበትን 1ኛ ዓመት ብሄራዊ በዓል አድርጋ ልታስብ ነው፡፡

ባለፈው ዓመት የአገሪቱ ጦር ክፍል አካል የሆነ ቡድን በፕሬዝዳንት ረጀብ  ጠይብ ኤርዶጋን ላይ  በፈፀመው የወታደራዊ መፈንቀለ መንግስት ሙከራ  የ260 ሰዎችን ህይወትን ቀጥፎ ነበር፡፡

ይሁንጂ መፈንቀለ መንግስቱ ሳይሳካ ቀርቶ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን እንዳስጠበቁ ይገኛሉ፡፡

ከመፈንቀለ መንግስቱ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የሚየገኙት ሀይማኖታዊ መሪና በቱርክ ውስጥ የሚገኘው ንቅናቀያቸው ተጠያቂ ቢደርግም እጄ የለበትም በሚል ሲያስተባብሉ ቆይተዋል፡፡

ይሁንእንጂ ከመፈንቀለ መንግስቱ ጋር በተያያዘ 150ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረዋል፣50ሺህ ገደማ ያህል ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል፡፡

አገሪቱ በወሰደችው እርምጃ  የሰብዓዊ መብት  ጥሰት ፈኝማለች በሚል  ክስ ቢቀርብባትም በተጨባጭ በመፈንቀለ መንግስቱ ውስጥ እጃቸው ባስገቡት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዷን ትከራከራለች፡፡

ከመፈንቀለ መንግስቱ በኋላ ለአንድ አመት በዘለቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ ላይ የምትገኘው ቱርክ፣ አሁን ለተጨማሪ 3 ወራት ልታራዝም እንደምትችል መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ላይ የቀጣው  የመፈነቀለ መንግስተ  ሙከራ በነገው እለት ድፍን አንድ አመቱን ይይዛል፡፡

ምንጭ ፡‑ ቢቢሲና ሲጂቲኤን