ሩስያ በአመታዊ የአየር ኃይል በዓሏ ከ15ዐ በላይ የጦር አውሮፕላኖች ትርዒት አሳይተዋል

ነሐሴ 07፣2009

ሩስያ በአመታዊ የአየር ኃይል በዓሏ ከ15ዐ በላይ የጦር አውሮፕላኖች ትርዒት ታይቷል፡፡

በተለይ ሱ3ዐ ፣ሱ 35፣ሚ26፣ካ52 እና ሚግ 29 የሚባሉ የጦር አውሮፕላኖች ከሞስኮ ወጣ ብሎ በሚገኘው የአርበኞች ፓርክ የአየር ላይ ትርዒት ለዕይታ በቅተዋል፡፡

ሩሲያ በ2ዐኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የተጠቀመችባቸው የተለያዩ ሞዴል የጦር አውሮፕላኖችም በትርዒቱ ላይ ታይተዋል ነው የተባለው፡፡

ትርዒቱን የሩሲያ ታዋቂ የአየር ላይ ትርዒተኞች ቡድን ናቸው ያቀረቡት፡፡

ላለፉት አሥራአንድ ዓመታት ሩሲያ የአየር ኃይል ቀኗን በየአመቱ በአውሮፓውያኑ ነሐሴ 12 አክብራለች፡፡

ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡