70 ከመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ስራቸውን በሮቦት እንዳይነጠቁ ይሰጋሉ

መስከረም 25፣2010

70 ከመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ስራዎቻቸው በሮቦቶች እንዳይነጠቁ ስጋት እንዳላቸው ተመለከተ።

ከአስርት አመታት ወዲህ በፋብሪካ የሚሰሩ ሰራተኞችን ተግባር ሮቦቶች ተክተው እየሰሩ እንደሆነ አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ᎓᎓

ከዚህ በመነሳት 70 ከመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን የምንሰራውን ስራ ሮቦቶች ይነጥቁን ይሆን ወደሚል ስጋት እየገቡ መሆናቸውን አንድ አዲስ ሪፖርት አሳይቷል᎓᎓

በሪፖርቱ እንደተመለከተው በሮቦት ላይ የሚሰሩ ተቋማት ስለ ሮቦቶች  ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥ ይጠበቅባቸዋል።

ፔው የጥናት ማእከል የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተው በአሜሪካ የሚካሄደው የቴክኖሎጂ ለውጥ በብዙዎቸ ዘንድ ጭንቀትን እየፈጠረ መጥቷል᎓᎓

3/4ኛ የሚሆኑ አሜሪካውያን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አብዛኞች ስራዎች ሮቦቶችና ኮምፒተሮች ተክተው እየሰሯቸው እንደሆነ ግንዛቤ እንዳላቸው ተናግረዋል᎓᎓ ይህ ግን ባብዛኛው ዜጋ አሉታዊ ተጽእኖ እያመጣና የኢኮኖሚ ልዩነቱን የከፋ እያባባሰው እንደሚመጣ ነው ስጋታቸውን መግለጻቸውን ደይልይ ሜል ዘግቧል።