5ዐዐ ኪሎ ግራም የምትመዝነው የዓለም ግዙፏ ሴት በህንድ ቀዶ ህክምና ሊደረግላት ነው

የካቲት 05፣  2009

5ዐዐ ኪሎ ግራም የምትመዝነው  የዓለም ግዙፏ ሴት በህንድ ቀዶ ህክምና ሊደረግላት ነው፡፡

የ36 አመቷ ግብፃዊት ኤማን አህመድ አብድ-ኤል ኢቲ ለ25 አመታት ከመኖሪያ ቤቷ ወጥታ አታውቅም ተብሏል፡፡

የደም መርጋትን ጨምሮ በተደራራቢ በሽታዎች በመጠቃቷ አሁን ሙምባይ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ክብደቷን የሚቀንስ ቀዶ ህክምና ሊደረግላት ነው፡፡

ኤማንን ከግብፅ ወደ ሙምባይ ለማድረስ ልዩ ቻርተር አውሮፕላን አስፈልጓል፡፡ ወደ ሆስፒታሉ ለማስገባትም የጭነት ማንሻ ክሬን ተጠቅመዋል፡፡

የክብደት ቅነሣ ቀዶ ህክምናው በልዩ የህክምና ክፍል እንደሚደረግ ሀኪሞቹ ገልፀዋል፡፡

ኢማን ባለባት ተደራራቢ በሽታ ቀዶ ህክምናው ፈታኝ እንደሚሆን ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ፥ ሮይተርስ