2016 ለሶሪያዊያን ህጻናት አስከፊው ዓመት ነው ተባለ

መጋቢት 4፣ 2009

በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ 2016 በህጻናት ሞት ቀዳሚ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ድርጅት አስታወቀ፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ በ2015 ከነበረው የህጻናት ሞት በ2016 በ20 በመቶ ጨምሮ 652 ደርሷል፡፡

ከእነዚህ ህጻናት ውስጥ 255 የሚሆኑት በትምህርት ቤታቸው አቅራቢያ የተገደሉ ናቸው፡፡

ይህ ቁጥር ጥናት የተረጋገጠ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቦ የመወች ህጻናት ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ ይችላል ብሏል፡፡

እንደ ዩኒሴፍ ገለጻ በ2016 ብቻ 850 ህጻናት ተገደው ወደ ጦርነት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ወደ ጦርነት የገቡት ህጻናት ቁጥር ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ያደገ ሲሆን ህጻናቱ በውጊያ ሜዳዎች ላይ ከመካፈላቸውም በላይ በአጥፎ ጠፊነት እንዲሰማሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ከስደስት ዓመት በፊት ሶሪያ ውስጥ የአገሪቱን ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድን በመቃወም የተነሳው ረብሻ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት መሸጋገሩ ይታወሳል፡፡