12ኛው የስልጤ ህዝብ ባህልና ቋንቋ አመታዊ ሲምፖዚየም ተካሄደ

ህዳር 24፤2010

12ኛው የስልጤ ህዝብ ባህልና ቋንቋ አመታዊ ሲምፖዚየም ተካሄደ፡፡

ባለፉት አመታት የስልጤ ህዝብ ባህልና ቋንቋን ለማልማትና ለማሳደግ በተደረጉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው በሲምፖዚየሙ ላይ  ተገልጿል፡፡

በበአሉ ላይ የታደሙ የህብረተሰብ ክፍሎች የስልጤ ህብረተሰብ ህገ-መንግስቱ የሰጠውን መብት ተጠቅሞ ባህሉን ማዳበር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የሃገሪቱ ህገ-መንግስት ለብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁለንተናዊ ዋስትና የሰጠ በመሆኑ ዜጎች ባህልና ቋንቋቸውን እንዲያ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩም ተጠቁሟል፡፡