ኢትዮጵያ ከቡና ኤክስፖርት 886 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ሐምሌ 06፤2009

ኢትዮጵያ ዘንድሮ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከቡና ኤክስፖት ለመጀመሪያ ጊዜ 886 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መግኘቷ ተገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ ገቢውን ያገኘችው በበጀት ዓመቱ ለዓለም ገበያ ካቀረበችው 221,000 ቶን ቡና እንደሆነ እና ከታቀደው 92 በመቶውን ማሳካት መቻሉን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ዘንድሮ የተገኘው ውጤት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በኤክስፖርት መጠን 11.5 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን በገቢ ረገድም 20 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ጀርመን፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ አሜሪካ፣ ቤልጄም፣ ሱዳን እና ደቡብ ኮሪያ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው 86 በመቶ ቡና ተቀባይ አገራት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከወርቅ ኤክስፖርት 74 ሚሊዮን ዶላር ያገኘች ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ከተገኘው 150 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነፃፀር በኮንትሮባንድ ምክንያት በግማሽ ቀንሷል፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ