ለስኳር ህመም የሚወጣው ወጪ በአመት 850 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል

ህዳር 5፤2010

በዓለም አቀፍ ደረጃ  ለስኳር ህመም የሚወጣው ወጪ በአመት እስከ 850 ቢሊዮን ዶላር  መድረሱ ተገለፀ፡፡

እ.አ.አ. ከ2000 ጀምሮ የስኳር ህሙማን ቁጥር በሶስት እጥፍ በመጨመሩ በአለም አቀፍ ደረጃ  በአመት ለመድሃኒቱ  የሚወጣውን  ወጪ  850 ቢሊዮን ዶላር  እንዳደረሰው የህክምና ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡

ከህሙማኖቹ  አብዛኖቹ ዲያቤትስ 2 በተሰኘ የስኳር ህመም የተያዙ  መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ህመሙ  ከውፍረት ፣ ከሰውነት እንቅስቃሴ  ማነስ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የዘርፉ ባለሙዎች ይናገራሉ፡፡

ከአለም አቀፍ የስኳር ፌዴሬሽን የወጣው መረጃ እንዳስታወቀው በአለም አቀፍ ደረጃ ከ11 አዋቂዎች መካከል አንዱ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከፍተኛ ስለሚሆን የስኳር  በሽታ የመያዝ እድሉ የሰፋ ነው፡፡

የህመሙ መስፋፋት በዚሁ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ በአሁኑ ሰዓት 451 ሚሊዮን የነበረው የስኳር ህመምተኞች ቁጥር እ.አ.አ. በ2045 693 ከፍ ሊል  እንደሚችልም ተገምቷል፡፡      

ምንጭ፡ ፎርቹን