አዲሱ የኢትዮጵየ አየር መንገድ ቦይንግ 787-9 አውሮፕላን ወደ ናይጀሪያ በረራ ጀመረ

ጥቅምት 29፣2010

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የገዛውን ቦይንግ 787-9 የተባለ እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላን ወደ ናይጄሪያ በረራ ጀመረ፡፡

‎‎

የተሻለ ነዳጅ ቆጣቢ እንደሆነ የተነገረለት ይህ አውሮፕላን 177 መንገደኞችን በማጓጓዝ ነበር በረራውን ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያ አቡጃ ከተማ ያካሄደው፡፡

አውሮፕላኑ ‹‹ናምዲ አዚኪዌ››  አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም ደማቅ አቀበባል እንደተደረገለት ተነግሯል፡፡

አየር መንገዱ ለአፍሪካ ደንበኞቹ የተሻለና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት አውሮፕላኑ መግዛቱን በናይጄሪያ አየር መንገዱ የትራፊክና የሽያጭ ስራ አስኪያጅ ፍሬህይወት መኮንን ተናግረዋል፡

ቦይንግ 787 አውሮፕላን ከሌሎች አውሮፕላኖች ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ድምጽ የሚያወጣና የተሻለ ነዳጅ ቆጣቢ መሆኑ እንዲሁም ውጪያዊ አካባቢዎችን መመልከት የሚያስችል ሰፋፊ የመስታወት መስኮት ያሉት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል፡

በአለም አውሮፕላኑን ገዝታ በመጠቀም ኢትዮጵያ ጃፓንን ተከትላ ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ ከ1960 ጀምሮ ወደ ናይጄሪያ በረራ የጀመረ ሲሆን፤ በአሁን ወቅትም በ5 የሀገሪቱ ከተሞች አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

ቦይንግ 787 አውሮፕላን በአሁን ወቅት በመብረር ላይ ካሉ አውሮፕላኖች እጅግ ዘመናዊው እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2011 ጀምሮ ከ600 በላይ የሚሆኑ እነዚህ አውሮፕላኖች ወደ ገበያው በመቀላቀል 200 ሚሊዮን ሰዎችን አጓጉዘዋ ነው የተባለው፡፡

በዚህም 19 ቢሊዮን ፓውንድ ገደማ የሚሆን ነዳጅ መቆጠብ እንደተቻለ ተጠቅሷል፡፡

ምንጭ፦ ሊደርሺፕ ድረ-ገጽ