በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ውጤታማ የሆኑ 641 አርሶና አርብቶ አደሮች፣ እንዲሁም ተመራማሪዎች ተሸለሙ

ህዳር 10፣2010

በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ውጤታማ ለሆኑ 641 አርሶና አርብቶ አደሮች፣ እንዲሁም ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች  ከፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ  እውቅናና የማበረታ ሽልማት  ተሰጣቸው ።

ተሸላሚዎቹ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ተጨባጭ ለውጥ ያመጡ እሴት የጨመሩና ለዜጎች  የስራ ዕድል የፈጠሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ተሸላሚዎቹ ልምዳቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ፍቃ በየነ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡