972 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጣ

ሐምሌ 01፤2009

በ4ዐ/6ዐ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሐ ግብር የመጀመሪያዎቹ 972 መኖሪያ ቤቶች በይፋ ዕጣ ወጣላቸው፡፡

ከወጣው እጣ ውስጥ 20 በመቶ ለመንግስት ሰራተኞች፣ 3 በመቶ ደግሞ ለዲያስፖራ ቅድሚያ እንደተሰጠ ተገልጿል፡፡ 

በአዲስ አበባ ማዛጋጃ ቤት እጣ የወጣላቸው ለ972 ቤቶች፣ 320 የንግድ ቤቶች ሲሆን  በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቤቶቹ ለባለ እድሎች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡

በ40/60 የቤቶች መርሀ ግብር 140 ሺህ ሰዎች እየቆጠቡ ሲሆን በእጣ የተካተቱት ከ18 ወራት በፊት የቤቶቹ ዋጋ ሙሉ በሙሉ የቆጠቡ መሆናቸው ተገልጿል።

ተጨማሪ 2ዐ ሺህ ቤቶችም በሚቀጥለው አመት ይጠናቀቃሉ ተብሏል፡፡