በሴራሊዮን በቁፋሮ የተገኘ የተፈጥሮ አልማዝ ኒዎርክ ላይ በ6.5 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

ህዳር 26 ፣2010

በሴራሊዮን በቁፋሮ በአንድ ፓስተር የተገኘ አልማዝ በትላንትናው እለት በኒዩዎርክ በተካሄደ ጫረታ በ6.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተሽጧል፡፡

በቁፋሮ የተገኘው ይኸው የአልማዝ ማዕድን  709 ካራት በመሆኑ በትልቅነቱ የመጀመሪያው ላይ ተቀምጧል፡፡ የሰላም አልማዝ  የሚል ቅፅል ስያሜ ማገኘቱም ተመልክቷል፡፡

ከአልማዙ ሽያጭ ከተገኘው አጠቃይ ገቢ 3.8 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው አልማዙ የተገኘበትን የአነስተኛ መንደር  ማህበረሰብ  ነዋሪዎችን  ተጠቃሚ ለማድረግ  ለመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ፈንድ እንዲሆን አልማዙን በቁፋሮ ያገኘው ፓስተር ሰጥቷል፡፡

ፓስተሩ አልማዙን በህገ ወጥ መንገድ ከመሸጥ ይልቅ ለሴራሊዮን መንግስት ሰጥቶ ለልማት እንዲውል በማድረጉ ሙገሳ ቀርቦለታል፡፡ ለዚህም ሲባል ነው የአልማዙ ስያሜ የሰላም አልማዝ የተባለው፡፡

የሴራሊዮን መንግስት በበኩሉ ከአልማዙ ሽያጭ የተገኘውን  ገቢ  አልማዙ የተገኘበትን የኮረያረዱ  መንደር    የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልን  ጨምሮ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ለኤሌክትሪክ፣ለመንገድ፣ ለህክምና እንክብካቤ ፣ለትምህርት ቤቶች ግንባታ እና እድሳት  እንደሚያውለው አስታውቋል፡፡

አልማዙ በከፍተኛ ዋጋ መሸጡ  ሌሎችም  ከመንግስት ጋር እንዲሰሩ ያበረታታል ተብሏል

ምንጭ፡- ቢቢሲ