ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ4.4 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አገኘች

ግንቦት 10፣ 2009

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ለጤና የልማት ስራዎች የሚውል የ4.4 ቢሊዮን ብር ብድር እና ስጦታ አግኝታለች፡፡

ከዚህ ውስጥ 3.4 ቢሊዮን ብር በብድር መልክ የተሰጠ ሲሆን ቀሪው በስጦታ መልክ የቀረበ ነው ተብሏል፡፡

ድጋፉ የተደረገው የሀገሪቱን የጤና ልማት ግቦች ለማስፈፀም መሆኑን የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር የላከው መግለጫ ያስረዳል፡፡

በተለይ ድጋፉ በእናቶች እና ህፃናት ጤና ላይ ለመስራት ትኩረቱን ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያቀደችው ዘላቂ የጤና ግብ በዓለም ባንክ ዕምነት ተጥሎበታል፡፡

የዓለም ባንክ ድጋፍ በአሜሪካ ዶላር 190 ሚሊዮን መሆኑን ከመግለጫው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡