ቻይና በሰአት 250 ኪ.ሜ የሚጓዝ ባቡር ሙከራ አደረገች

ህዳር 13፡2010

በሰአት 250 ኪሎ ሜትር እንደሚጓዝ የተገመተው የቻይና ፈጣን ባቡር በከፊል አቅሙ የመጀመሪያ ሙከራ አደረገ፡፡

ባቡሩ የመጀመሪያ ሙከራውን ያደረገው ሺያን ከተባለው የሰሜን ምእራብ የአገሪቱ ክፍል ተነስቶ እስከ ደቡባዊ ምእራብ ቻንግዱ ድረስ ነው፡፡

ባቡሩ የሙሉ መስመር ሙከራ ከማድረጉ በፊት አጫጭርና ተከታታይ ሙከራዎች ማድረጉም ተገልጿል፡፡

ይህ 643 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የባቡር መስመር ከቻንግዱ እስከ ሺያን 16 ሰአታት ይፈጅ የነበረውን ጉዞ ወደ 3 ሰአታት አሳጥሮታል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ