ከከባድ ሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የ210 ግለሰቦች ንብረት በፍርድ ቤት ታገደ

ነሀሴ 4 ፤2009

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦችና ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የ210 ግለሰቦች ንብረት በፍርድ ቤት ታገደ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ግለሰቦቹ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር በተያያዘ 15 ኩባኒያዎች ታግደዋል፡፡

ከከእነዚህ መካከልም አሰር ኮንስትራክሽን፤ ዲኤምሲ ኮንስትራክሽን፤ ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን፤ ቲና ኮንስትራክሽን፤ የማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ፤ ትራንስ ናሽናል ኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ፤ ሃይሰም ጠቅላላ ኢንጂኔሪንግ፤ከማኒክ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ ጂንግ ሊንግ ኢንተርናሽናል ኢንጂኔሪንግና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ከወንጀሉ ተጠርጣሪዎች መካከል ተጨማሪ አንድ ግለሰብ ከፌደራል መንገዶች ባለስልጣን በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በአጠቃላይ የተያዙት ሰዎች ቁጥርም 54 መድረሱን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡