ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ፓርኮቿን ቁጥር በ2010 15 ለማድረስ አቅዳለች

ሃምሌ 6፤2009

ኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግና ኤክስፖርት ዘርፏን ለማሳደግ እስከ ጥር 2010 ድረስ ያሏትን የኢንደስትሪ ፓርኮች ቁጥርን ወደ 15 ለማድረስ ማቀዷ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንደስትሪያል ፓርክ ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አርከበ እቁባይ እንደገለጹት ከሆነ ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ፓርኮቿን ቁጥር ለማሳደግ ያቀደችው በፈረንጆቹ 2025 ድረስ የማኑፋክቸሪንግ ሴክተሩ ከሀገሪቱ አመታዊ ጥቅል ምርት 20 በመቶውን እንዲሁም ከኤክስፖርት መጠኑ ደግሚ 50 በመቶውን እንዲሸፍን ታስቦ ነው፡፡

በጥር 2010 የቂሊንጦ ፋርማሲቲካል እና ቦለ ለሚ ቁጥር 2 ኢንደስትሪያል ፓርኮች ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በግንቦት ወር 2010 ደግሞ የባህር ዳር እና የጅማ ኢንደስትሪያል ፓርኮች ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

 እንዲሁም በሰኔ 2010 የደብረ ብርሃንና አረርቲ ኢንደስትሪያል ፓርኮች ለምርት ዝግጁ ይሆናሉ የብለው እንደሚጠበቁ ዶ/ር አርከበ እቁባይ ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ እና የአዳማ ኢንደስትሪያል ፓርኮች በ190 ሚሊዮን ዶላር ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑ መንግስት ገልጿል፡፡

 ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ የሚገኙ ሰባት የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዳሏት ተናግረዋል፡፡.

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለ14 አመታት ያህል የባለሁለት ዲጂት የምጣኔ እድገት ለማስመዝገብ ያቀደች ሲሆን በመጀመሪያ አስርት አመታት ለሁለት ሚሊዮን ቀጥተኛ በሆነ መንገድ እንዲሁም 4 ነጥብ አራት ሚሊዮን ለሚሆኑት ዜጎች ደግሞ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የስራ እድል ለመፍጠር መታዱን አብራርተዋል፡፡

ምንጭ፡ ሺንዋ