በ2017 የብሪክስ አገራት የንግድ እንቅስቃሴ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ

ጳጉሜ 3፣2009

በብሪክስ አገራት መካከል በአውሮፓውያኑ 2017 ያለው የንግድ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን በአለም በትልቅነቱ ከታወቀ የዕቃ መጫኛ መርከብ የተገኘ አሃዝ አመልክቷል፡፡

በአለም አቀፍ ከ7 ዕቃ ጫኝ መርከቦች መካከል አንዱን የሚያስተናግደው ማርክስ ላይን ከቻይና ወደ ህንድ በመርከቦቹ የተጓጓዘው የዕቃ መጠን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በአመቱ አጋማሽ ላይ 26 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ገልጿል፡፡

ከቻይና ወደ ብራዚል እንዲሁም ከቻይና ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓጓዘው ዕቃ በ9 በመቶ ማደጉን ታላቁ የቻይና ክላስተር ማርክስ ላይን ዋና ስራ አስኪያጅ ማይክ ፋንግ  ተናግረዋል፡፡

ከደቡብ አፍሪካ ወደ ቻይና የተጓጓዘው የዕቃ መጠንም በተመሳሳይ ጊዜ በ44 በመቶ ማደጉ ተገልጿል።

ብሪክስ ብራዚል፣ሩሲያ፣ህንድ፣ቻይናና ደቡብ አፍሪካ ያቋቋሙት የንግድ ቀጣና ነው።

ምንጭ-ሮይተርስ