የሪዮ 2016 ኦሎምፒክ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ

ነሀሴ 16 ፣2008

ብራዚል ያዘጋጀችው የሪዮ 2016 ኦሎምፒክ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ


የ2020 የኦሎምፒክ አዘጋጅ የተመረጠችው የጃፓኗ ቶኪዮ የኦሎምፒኩን ሰንደቅ አላማ ተረክባለች፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር  ሽንዞ አቤም በምድረኩ ላይ ለየት ባለ  አቀራረብ መድረኩ  ላይ ተገኝተው ነበር።


ሶስት ሰዓት የፈጀው የሪዮ ኦሎምፒክ የመዝጊያ ስነ ስርዓት በብራዚል አርቲስቶች ደምቆና አሸብርቆ ነበር የተጠናቀቀው ፡፡
ለአስራ ስድሰት ቀናት በቆየው በሪዮ ኦሎምፒክ ከ206 ሀገራትና  ከስደተኞች ቡድን የተውጣጡ  11303 አትሌቶች ተሳትፈውበታል፡፡

በአለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የመዝጊያ ስነ-ስርዓቱን እንደተከታተሉትም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ባለፉት 16 ቀናት በሪዮ ኦሎምፒክ በተካሄዱ  ውድድሮች በርካታ  ታሪካዊ  ክስተቶች የተመዘገቡበት ሆኖ አልፏል።

ውድድሩን አሜሪካ በ47 ወርቅ አሜሪካ በበላይነት ጨርሳለች። ብሪታንያ በ27 ፣ቻይና  ደግሞ  በ26 ወርቅ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘው በበላይነት አጠናቀዋል።

በዚሁ  የሪዮ ኦሎምፒክ በሰባት የኦሎምፒክ  ስፖርት አይነቶች 27 ክብረ ወሰኖች ተመዝግበዋል።

በኦሎምፒክ ታሪክ 5 ጊዜ ተሳትፎው በግሉ 28 ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበው  አሜሪካዊ ዋናተኛ ማይክል ፊሊፕስና በሶስት የኦሎምፒክ መድርኮች በ100፣ 200፣ 4*100 የዱላ ቅብብል ውድድሮች በአያንዳንዱ  መድረክ በተከታታይ ሶስት ሶስት ሜዳሊያዎችን  በድምሩ ዘጠኝ ሜዳሊያ ያስመዘገበው ጃማይካዊ  ዩሲያን ቦልት ለቀጣይ ኦሎምፒክ ከወዲሁ እንደማይወዳደሩ ማሳወቃቸው ትልቅ መነጋገሪያ  ሆኗል።

በሪዮው ኦሎምፒክ ሌላው የተመዘገበው ታሪክ ፊጂ፣ዮርዳኖስና ኮሶቮ የመጀመሪያ  የኦሎምፒክ የወርቅ ታሪክ በሀገራት መዝገብ ማስፃፋቸው ነው።