ቻይና ለቀጣይ 20 አመታት ለአውሮፕላን ግዥ ከ1ትሪሊዮን ዶላር በላይ ልታወጣ ነው

ጰጉሜ 1፣2009

የቻይና አየር መንገድ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ በረራውን ለማስፋፋት በቀጣይ 20 አመታት በ1.1 ትሪሊዮን ዶላር ከ7ሺህ በላይ አውሮፕላኖችን እንደሚገዛ ቦይንግ  አስታውቋል፡፡ 

የቦይንግ የንግድ አውሮፕላኖች የገበያ ምክትል ፕሬዝዳንት ራንዲ ቲንሴዝ እንደገለጹት አየር መንገዱ  እ.አ.አ. እስከ 2036 ድረስ ለመግዛት ያቀዳቸው 7ሺህ 240 አውሮፕላኖችን ባለፈው አመት ለመግዛት ከታቀዱ 6810 አሜሪካ ሰራሽ አውሮፕላኖች በ6.3 በመቶ ይበልጣሉ፡፡

የአሜሪካ ኩባኒያ በበኩሉ ለመግዛት ከታቀዱት 7,240 አውሮፕላኖች መካከል የሶስት አራተኛው ትዕዛዞች በቻይና እና በመላው እስያ ለመጓጓዠ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሟላትና የአውሮፕላን ፍሰቱን ለማሳለጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጿል፡፡