በሀረሪ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት መጠን 2.5 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

ህዳር 25፣2010

በሀረሪ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት መጠን  2.5 በመቶ መድረሱን የሃረሪ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጠጣሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ::

የሃረሪ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጠጣሪያ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ አፈንዲ ባሻ እንደተናገሩት ባለፉት አስር አመታት የስርጭት መጠኑን ለመቀነስ በተከናወኑ ተግባራት የስርጭት መጠኑ ከነበረበት 3.8 በመቶ ወደ 2.5 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡

ይህም  የሀረሪ ክልልን በሀገር አቀፍ ደረጃ 3ተኛ ከፍተኛ የስርጭት መጠን ያለበት እንዲሆን አድርጓታል፡፡

ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ቀድሞ የተሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመቀዛቀዛቸው መዘናጋት መፈጠሩን የገለጹት የሃረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አብዱማሊክ በከር ኤች አይ ቪ ኤድስ አምራች የሆነው ወጣቱን ሃይል በመጉዳት  ለልማት እንቅስቃሴ ማነቆ በመሆኑ በሃገር አቀፍ ደረጃ ቫይረሱን ለማጥፋት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት በተለይ ትምህርት ቤቶችና የሚዲያ ተቋማት በትኩረት  ሊሰሩ  ይገባል ብለዋል፡፡

ዘገባውን ያደረሰን የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ነው።