የአዘርባጃን መሪ ለቅንጦትና ለጉቦ ከ2.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከፍለዋል ተባሉ

ነሃሴ 30፤2009

በስልጣን ላይ የሚገኙት የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት ልሃም አሊዬቨ በሁለት አመታት ውስጥ ለአውሮፓዊያን ፖለቲከኞች ማባበያ ለቅንጦች እቃ መግዣ በሚስጥር 2.8 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ መፈጸማቸውን የተካሄደባቸው ምርመራ ይፋ አድርጎታል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ገንዘቡን ያስተላለፉት በእንግሊዝ ድብቅ የማገበያየት ስራን በሚያከናውኑ አራት ኩባኒያዎችን በመጠቀም ነው ተብሏል፡፡

የማባበያ ገንዘቡ ተከፋይ ከሆኑት ግለሰቦች መካከልም ለአውሮፓ ህብረት የተለያዩ ቀና ፖለቲካዊ ጽንሰ ሃሳቦችን የሚያፈልቁ ፖለቲከኞች እንደሚገኙበት ነው የተነገረው፡፡

የገንዘቡ ተቀባዮች በሙሉ የተሰጣቸው ገንዘብ ምንጩ ከዬት እንደሆነ እንኳን ስለማወቃቸው ምንም ተጨባጭ መረጃ እንደሌላቸው ነው የተብራራው፡፡

በጉዳዩ ላይ የተደረገው ምርመራ እንዳመለከተው እ.አ.አ. ከ2014 ጀምሮ ለሁለት አመታት የወጣው ሚስጥራዊ ወጪ አዘርባጃንን ማራቆት በሚል ቅጽል ስም ይታወቃል፡፡

ለማባበያና ቅንጦት እቃዎች ወጪ ተደረገ የተባለው ይህ ገንዘብ የሀገሪቱ መንግስት በዜጎቹ ላይ ኢሰብዓዊ ጉዳት እያደረሰባቸው ነው ተብሎ ለአውሮፓ ህብረት ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ምክር ቤት የቀረበው ሪፖርት እንዳይጸድቅ የተሰጠ ነው ተብሏል፡፡

ይፋ በተደረገው ጥናት ዙሪያም ከአዘርባጃን መንግስት እስካሁን የተሰጠ ማስተባበያ የለም፡፡

ምንጭ-ቢቢሲ