የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅቱ ሠራተኞች ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የ2.2 ሚሊየን ብር ቦንድ ገዙ

ነሐሴ 13፣2009

የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሠራተኞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ የሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ ስምንት  ሺ ብር የቦንድ ግዢ ፈፀሙ፡፡

ሠራተኞቹ የቦንድ ግዢውን የፈፀሙት የአንድ ወር ደሞዛቸው ለግድቡ ግንባታ እንዲውል በመወሠን ነው፡፡

የድርጅቱ ሠራተኞች በቀጣይም ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን ድርጅት በላከልን መረጃ አመልክቷል፡፡