ናይጀሪያ የሃይል እጥረቷን ለመቅረፍ 15.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

ጥቅምት 13፣2010

ናይጀሪያ በቀጣይ 3 ዓመት ውስጥ የሃይል እጥረቷን ለመቅረፍ 15.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት የሀገሪቱ የሃይል ሚኒስትር ገለጸ፡፡

ለዘርፉ ዕድገት ደጋፊ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ የፌደራል መንግስቱን እና የግል ዘርፍን ሀብትን ለሃይል አቅርቦት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

በናይጀሪያ የህዝቡ የሃይል ፍላጎት እና አቅርቦት ሰፊ ልዩነት እንዳለው ዘገባው አትቷል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ 3 ዓመታት የሃይል መሰረተ ልማት ግንባታውን በፍላጎት ልክ ለማድረስ 15.6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ተብሏል፡፡

ገንዘቡ ለአዳዲስ የሃይል ምንጮች ግንባታ እና ነባሮችን ለማሸሻል ጥቅም ላይ እንደሚውልም ተገልጿል፡፡

በዘርፉ ባለሃብቶችን ለመሳብ ማበረታቻ እና ሳቢ ፖሊሲ ሊኖር እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡

ዘገባው የዘ ጋርዲያን ነው፡፡