የአፍሪካዊዩ ባለፀጋ በናይጀሪያ በ150 ሚሊዮን ዶላር የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

ነሐሴ 05፣2009

የአፍሪካዊዩ ባለፀጋ አሊኮ ዳንጎቴ በናይጀሪያ በ150 ሚሊዮን ዶላር የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ሊገነባ  መሆኑን አስታወቀ፡፡

ከአፍሪካ ግንባር ቀደሙ ባለፀጋ የሆነው አሊኮ ዳንጎቴ በሰሜናዊ ናይጀሪያ 100 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የፀሀይ ኃይል ፕሮጀክት ለመገንባት ከካኖ ግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር የመግባባያ ስምምነት ተፈሯርመዋል፡፡

የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሮጀክቱን ከብላክ ሪኖ ኩባንያ ጋር ተጣምሮ ነው እውን ለማድረግ እየሰራ ያለው ተብሏል፡፡

የፀሀይ ሀይል ፕሮጀክቱ መስራት የሰሜዊ ናይጀሪያን የኢዱስትሪ እድገት የበለጠ ለማሳደግ ሁነኛ ሚና ይጫወታል ተብሏል፡፡

የአሊኮ ዳንጎቴ ኩባንያዎች ቡድን ስብስብ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ዳይሬክተር  ኢንጂነር  መንሱር አህመድ በኃይል ልማት ዘርፍ በመላው አለም ጭምር የተሻለ ውጤት እንዲገኝ መስራት እንፈልጋን ብለዋል፡፡

እንደ ሲቲጂኤን ዘገባ የካኖ ግዛት እንዲሁም መላው ናይጀሪያ በኃይል አቅርቦት እጥረት የምጣኔ ሀብት ዘርፉን በተፈለገው ለማሳደግ እንቅፋት እንደሆነ ይነገራል፡፡

ናይጀሪያ በአሌክትሪክ እጥረት 95 ሚሊዮን የሚጠጋው  ህዝቧ የኃይል አቅርቦት የለውም፡፡

ናይጀሪያ በአሁኑ ጊዜም ከ5ሺህ ሜጋ ዋት የማይበልጥ ኃይል  አቅርቦት ይዛ ነው  ከአፍሪካ ግዙፍ የኢኮኖሚ ደረጃን የያዘችው፡፡

ምንጭ፡‑ ሲጂቲኤን