ቢል ጌትስ ለኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መከላከያ መድሃኒት ለመፈብረክ 140 ሚሊዮን ዶላር መደበ

ታህሳስ 26፣2009

አሜሪካዊው ቢሊዬነር ቢል ጌትስ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መከላከያ መድሃኒትን ለመፈብረክ ለሚደረገው ምርምር 140 ሚሊዮን ዶላር መመደቡ ተነግሯል፡፡

ይህ አዲስ የምርምር ሃሳብ ከዚህ በፊት ሲሰጥ የነበረውን የህክምና ዘዴ  የሚቀይር ሲሆን በክርን ውስጥ የሚቀበር ስለመሆኑ ይፋ ሆኗል፡፡

ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለዚህ አስደናቂ ነው ለተባለለት የህክምና ምርምር አስፈላጊውን ወጪ ይሸፍናሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ያለው የበሽታው መከላከያ ዘዴ በየቀኑ በእንክብል መልክ የሚወሰድ ሲሆን የአለም ጤና ድርጅት ይህን መድሃኒት እንዲወስዱ የሚመክረው በተለያየ ምክንያት ለበሽታው የከፋ ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች ብቻ ነው፡፡

ልክ እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያ የሚያገለግለው ይህ አዲስ የህክምና ቴክኖሎጂ ክኒኑን በየቀኑ በመውሰድ የሚፈጠረውን መሰላቸት ይቀንሳል ነው የተባለው፡፡

ቴክኖሎጂው አንዴ ክርን ውስጥ ከተቀበረ ለ12 ወራት የሚያገለግል ሲሆን በቀላሉ ቀዶ ጥገና ሳያስፈልግ እንደገና መሞላት እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ- ኢኮኖሚክ ታይምስ