ዳንጎቴ በናይጄሪያ የተመጣጠነ ምግብ ለማቅረብ 100 ሚሊዮን ዶላር ሊሰጥ ነው

ጥቅምት 27፣2010

የአሊኮ ዳንጎቶ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የምግብ እጥረት ላለባቸው የናይጀሪያ ዜጎች የሚውል 100ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው፡፡

አፍሪካዊ ቁጥር አንድ ባለፀጋ ዳንጎቴ በናይጀሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ እና ምዕራብ ግዛቶች የተመጣጠነ ምግብ የማያገኙ ዜጎችን ቁጥር በ60 በመቶ ለመቀነስ እንደሚሰራ የአገሪቱ ቫንጋርድ ጋዜጣ ዘገባ አትቷል ፡፡

በዓለማችን በየዓመቱ ህይወታቸው ከሚያልፉ ህጻናት መካከል ግማሾቹ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ለህልፈት እንደሚዳረጉ ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ ደግሞ  ናይጀሪያ ችግሩ የሚበዛባት ሀገር መሆኗን   ዘገባው ያስርዳል፡፡

በናይጀሪያም በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን ህጻናት ግማሽ ያህሉ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት 5 ዓመት ሳይደርሱ ህይወታቸው ያልፋል፡፡

በአገሪቱ 11 ሚሊዮን ህጻናትም በዚህ ምክንያት ደካማ ቁመና ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ህጻናት በመጀመሪያዎቹ 1ሺህ ቀናት ተመጣጣኝ ምግብ ማግኘት ቢኖርባቸውም በታዳጊ ሀገራት ይህን ማድግ ከባድ ሆኗል፡፡

ምንጭ፡‑ ቫንጋርድ ናይጄሪያ