ኢትዮጵያ የ125 ሚሊየን ዩሮ የብድርና ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች

መስከረም 06፣2010

ኢትዮጵያ ከጣልያን መንግሥት ጋር የ125 ሚሊየን ዩሮ የብድርና ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች፡፡

ስምምነቱ በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ለግብርና ልማት፣ለመሠረታዊ አገልግሎቶች እና በሥራ እድል ፈጠራ ኢትዮጵያን የሚደግፍ ነው ተብሏል፡፡

ከተገኘው ብድርና ድጋፍ ለግብርና ልማት 64 ሚሊየን ዩሮ፣ ለትምህርት፣ ለጤናና መሰል መሠረታዊ ግልጋሎቶች 44 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮ እንዲሁም ለመልካም አስተዳደርና ለሥራ እድል ፈጠራ 16 ነጥብ 1 ሚሊየን ዩሮ እንደሚውል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ አድማሱ ነበበ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር ጁሴፔ ሚስትሬታ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ስደትን ለመግታት ለወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት እንዲሁም ለምታከናውናቸው ሌሎች የልማት ሥራዎች የጣልያን መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ሪፖርተር፣ ነፃነት ወርቁ