የደቡብ ክልል ባካሄደው የጥልቅ ተሃዲሶ ግምገማ 1ሺ 9መቶ ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት አነሳ

የካቲት፣ 7 2009

የደቡብ ክልል ባካሄደው የጥልቅ  ተሃዲሶ ግምገማ 1ሺ 9መቶ  ሀያ ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ ።

የክልሉ  ምክር ቤት አራተኛ መደበኛ  ጉባኤውን  በማካሄድ ላይ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ  ዳልኬ   ባለፉት ስድስት ወራት የጥልቅ ተሃድሶ  መድረኮችንና  የትራስፎርሜሽን  አጀንዳዎችን  ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ርብርብ መደረጉን ተናግረዋል።

የክልሉ  መንግስት የ15 አመታት የተሃድሶ  ጉዞውን  ከከፍተኛ   አመራር በመጀመር  እስከ   ህዝቡ   የዘለቀ  በጥልቀት  የመታደስ   ትግል መደረጉንም ገልፀዋል።

በሂደቱ  በሁሉም  ደረጃ  የሚገኙ 496 ሺህ 311  አመራሮች እንዲያልፉ  ተደርጎ  1ሺ 9መቶ  ሀያ ከፍተኛ አመራሮችና 18 ሺህ253 መካከለኛ  አመራሮች ከኃላፊነት  እንዲነሱ መደረጉን አስረድተዋል።

የህዝብ ጥያቄዎችን  በመለየት  በህዝብ የተደራጀ   ተሳትፎ  ለመፍታት በተደረገው ጥረትም  የተለያዩ  እርምጃዎች  መወሰዳቸው ተመልክቷል።

ርዕሰ  መስተዳደሩ  ባቀረቡት ሪፖርት በህብረተሰቡ ውስጥ  ቅሬታና የመልካም  አስተዳደር  ቅሬታ   እየፈጠሩ   ባሉ  የመሬት አስተዳደር ሙያተኞችና ኃላፊዎች ፣ የህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃ በተጠቀሙ ፣ የተመዘበረ የመንግስትና የህዝብ  ገንዘብ  ለግላቸው ባዋሉ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዷል።

ጉባኤው በዛሬው ውሎ  የርዕሰ መስተዳደሩን  ሪፖርት ካደመጠ  በኃላ በተለይም    በግብርው ዘርፍ ፣በገቢ አሰባሰብና በከተሞች የመልካም አስተዳደር ላይ በተገኙ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ማድረግ ጀምሯል።

ምንጭ፥  የደቡብ ሬድዮና  ቴሌቭዥን ድርጅት