ህገ-መንግስቱ ለፀደቀበት 23ተኛ ዓመት ፕ/ት ሙላቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ህዳር 28፣2010

የብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል መላዉ የአገሪቱ ህዝቦች በጋራ እየገነቡት ያለዉ የፌዴራሊዝም ስርዓት በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተለመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ህዳር 29 ህገ-መንግስቱ የፀደቀበትን 23ተኛ ዓመትና 12ተኛዉን የብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

ዜጎች በህገ-መንግስቱ ላይ ያላቸዉን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራትን በማጠናከር የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡