የ12ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል አካል የሆነው ሲምፖዚየም በሰመራ ከተማ ተጀምሯል

ህዳር 28፣2010

የ12ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል አካል የሆነው ሲምፖዚየም በሰመራ ከተማ ተጀምሯል፡፡

በሲምፖዚየሙ ላይ የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች ዕንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ ስዩም አወል የበዓሉ መከበር የህዝቦችን አብሮነት ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ያለው አባተ በበኩላቸው በእንደዚህ ዓይነት ሲምፖዚየም የሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሁፎች  የህገ-መንግስት አስተምህሮ በበዓላት ወቅት ብቻ የተወሰነ እንዳይሆን በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ ለመስራት ዝግጅቱ ተጠናቋል ብለዋል፡፡