የመጀመሪያው አጭር የጽሁፍ መልዕክት ከተላከ ዛሬ 25ኛ አመቱን ይዟል

ህዳር 24፤2010

በዓለማችን የመጀመሪያ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከተላከ እነሆ ዛሬ 25ኛ አመቱን አስቆጥሯል፡፡

በእንግሊዝ ሃገር በዚህ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያውን አጭር የጽሁፍ መልዕክት የላከው የ22 ዓመቱ ኒል ፓፕዎርዝ የተባለ ኢንጂነር ነበር፡፡

አጭር የጽሁፍ መልዕክቱም "መልካም ገና" የሚል ሲሆን መልዕክት ተቀባዩ ደግሞ በወቅት የቮዳፎን ኩባንያ ዳይሬክተር የነበረው ሪቻርድ ጃርቪስ ነበር፡፡

ቮዳፎን የተባለው የቴሌኮም ኩባንያ ይህንን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል ፈር ቀዳጅ ሲሆን የፊንላድ ኢንጅነር ማቲ ማኮነን ደግሞ ቴክኖሎጂውን በማሻሻል ለተጠቃሚዎች ቀላል አድርጎታል፡፡

አሁን በስልክ ተጠቃሚዎች ዘንድ የሚዘወተረው እንደ ዋትስአፕ እና አይ ሜሴጅ ያሉ የአጭር ዕሁፍ መልዕክት መለዋወጫ ሶፍትዌሮች መነሻቸው ከዚሁ ኒል ፓፕዎርዝ ፈጠራ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡ ሚረር