በሰሜን አሜሪካ 80 በመቶ ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ተጠቆመ

ህዳር 12፣2010

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በሰሜን አሜሪካ በክረምት ወራት ከሚዘንበው መደበኛው ዝናብ 80 በመቶ ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ባለሞያዎች አስጠነቀቁ።

በአሜሪካ በቅርብ አመታት በሚጥለው ከፍተኛ ዝናብ በጎርፍ የመጥለቅለቅ ሁነቶች እየታዩ ነው። በአውሮፓውያኑ 2010 በምዕራብ ቨርጂንያ እንዲሁም በ2016 በሎውሲና ያጋጠሙት የጎርፍ አደጋዎች ይጠቀሳሉ።

በአሜሪካ በጎርፍ አደጋ በአመት እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚወጣም መረጃዎች ያመለክታሉ።

የአየር ንብረት ለውጥ ሳይንቲስት አንደርሰን ፕሬን የአየር ልቀት መጠኑ ካልቀነሰ በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ ላይ እንዲህ አይነት ክስተቶች እየተባበሱ ሊሄዱ  እንደሚችሉ ገልጸዋል።

አደጋው ከምገመተውና ከምታሰበው በላይ እየጨመረ ነው ብለዋል ሳይንትስቷ፡፡

በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ የአየር ሙቀት መጨመር ምክንያት የአሜሪካ ደቡባዊ ክፍል የዝናብ መጠን አሁን ካለው ከ80 በመቶ በላይ ሊያሳድገው እንደሚችልም ተገልጿል።

ምንጭ፣ ዘ ኢንዲፔንደንት