የብአዴን 37ኛው የምስረታ በዓል በባህርዳር ለታጋዮች እውቅና በመስጠት ተከብሯል

ህዳር 11፣2010

የብአዴን 37ኛው  የምስረታ በዓል በባህርዳር ለታጋዮች እውቅና በመስጠት ተከብሯል።

እውቅናው የተሰጣቸው የድርጅቱ ታጋዮች እስከ ግንቦት 20/1983 ዓ.ም ድረስ የደርግን አገዛዝ ለመጣል በተደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ  ያበረከቱ  ታጋዮች ናቸው።

በዚህም በከተማዋና በአከባቢው የሚገኙ 634 ታጋዮች የእውቅና ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።