በዚህ ዓመት 30 ሺህ ቱሪስቶች ጎንደር ከተማን ጎብኝተዋል

ህዳር 5፤2010

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች በዘንድሮው የመጀመሪያ ሩብ አመት በ30ሺ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች መጎብኘታቸውን የከተማው ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ፡፡

የውጪ ሀገር ቱሪስቶች በበኩላቸው ታሪካዊና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ያለአንዳች ስጋት መጎብኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ በክልሉ የሰፈነው ሰላም በሁሉም የክልሉ የቱሪስት መዳረሻዎች የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብሏል፡፡