አሊባባ በቀን ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ በማስመዝገብ ክብረ ወሰኑን ሰብሯል

ህዳር4 ፤2010

በኢንተርኔት ግብይት የሚታወቀው የቻይናው ኩባንያ አሊባባ በአንድ ቀን  ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ በማስመዝገብ ክብረ ወሰን የሰበረ ግብይት ፈፅሟል፡፡

አሊባባ ባለፈው አመት ከነበረው የ18 ቢሊዮን ዶላር ዕለታዊ ሽያጩን በማሻሻል  በ7 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ በማሳየት ነው የዘንድሮውን ስኬታማ የኢንተርኔት ግብይት የፈፀመው፡፡

የአሊባባ 90 በመቶ የሚሆኑት ደንበኞች ከ200 በላይ ከሚሆኑ አገራት ነው የኢንተርኔት ግብዩቱን በሞባይል በመታዝ የፈፀሙት፡፡

በኢንተርኔት አገበያይ ኩባንያዎች እ.ኤ.አ ህዳር ወር በገባ በ11ኛው ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ  ከሌሎች ጊዚያት በተሻለ ሽያጭ የሚያስመዘግቡበት ዕለት ነው፡፡

የቴክኖሎጂው መዘመን የሽያጭ ስርዓቱን ቀላል እያደረገው መጥቶ የኢትርኔት ግብይት ስርዓቱ ልዩነት ፈጣሪ እንዲሆን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የሲጂቲኤን ዘገባ አመልክቷል፡፡

ይህም ለቻይና ኢኮኖሚ ከፍተኛ እንድምታ እንደሚኖረው ተመልክቷል፡፡

አሊባባ በቻይናዊ ስራ ፈጣሪ ጃክ ማ አማካኝነት የተመሰረተ ኢንተርኔትን መሰረት በማድረግ የአለም ገበያን እየመራ ያለ ኩባንያ ነው፡፡