በኮንጎ ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት ከ70ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

ጥቅምት 29፣2010

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት ከ70ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን  /ዩ. ኤን. ኤች. ሲ. አር/ ገለጸ።

ኮሚሽኑ ተፈናቃዮቹ ቅድሚያ የምግብ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ መጠለያና ከለላ እንደሚያስፈልጋቸውም ገልጿል።

3.9 ዜጎቿ የተፈንናቀሉባት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከአፍሪካ በብዛት የተፈናቀሉባት አገር ሆናለች።

አገሪቱ 8 ነጥብ 5 አምስት ሚሊዮን ዜጎቿም ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች እየተከሰተ ባለው ግጭትና አለመረጋጋት የተፈናቃዮች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ስጋት መኖሩን የሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ አመልክቷል።