በሶማሊያ በደረሰ የቦምብ ጥቃት የ230 ሰዎች ህይወት አለፈ

ጥቅምት 05፣2010

ጥቅምት 4/2010 ዓ.ም በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃድሾ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመዱ ቦምቦች በተፈጸሙ  ጥቃቶች ቢያንስ የ230 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአገሪቱ ባለልጣናት ገለጹ።

በከተማዋ ሰዎች በብዛት በሚንቀሳቀሱበት አከባቢ  በተፈጸመ  የቦምብ  ጥቃት  ቢያንስ 230 ሰዎች ሞሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል። በርካቶች መጎዳታቸውን የገለጸው የአገሪቱ  ፖሊስ የሞቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።

እስከ አሁን ለጥቃቱ ሀለፊነቱ የወሰደ አካል አለመኖሩን ያመለከተው የቢቢሲ ዘገባ ሀገሪቱ በተደጋጋሚ  የአልሸባብ ጥቃት ኢላማ ሆና መቆየቷን አስታውሷል።

ጥቃቱን ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ተጎጂዎችን ለማሰብ የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አውጀዋል።

ጥቃቱ በሶማሊያ ከ1ዐ ዓመታት በኋላ አስከፊው ነው ተብሏል፡፡