የዋቻ ፣ ማጂ የ17ዐ ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ሳይጠናቀቅ ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተነገረ

ጥቅምት 2፤2010

ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ የተገነባው የዋቻ ማጂ የ17ዐ ኪሎ ሜትር መንገድ 3 ዓመት ሳያገለግል በመበላሸቱ መቸገራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የመንገዱ ግንባታ ሳይጠናቀቅ መንገዱ መፈራረሱንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

የዋቻ ማጂ ማጂ መንገድ ከፍተኛ የሕዝብ ሀብት ቢወጣበትም በግንባታ ጥራት ምክንያት ለሕብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ብለዋል የቤንች ማጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወንድሙ ገብሬ፡፡

ተቋራጩ አካባቢውን ለቆ ቢወጣም እስከአሁን መንገዱ ይፋዊ ርክክብ አልተደረገለትም ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሊሰጡን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሁለት የስራ ኃላፊዎች በኢቢሲ እስቱዲዮ በመገኘት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡