በመጪው ምርት ዘመን 55 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱ ተነገረ

ጥቅምት 01፤2010

ለቀጣዩ የምርት ዘመን የታቀደው ተጨማሪ 55 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲሳካ ለኩታገጠም እርሻ ትኩረት መሰጠቱን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት በ2ዐዐ9/1ዐ የምርት ዘመን የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን የሚገመግም መድረክ እያካሄደ ነው፡፡