በተያዘው ዓመት ከ22 ሺ በላይ ተማሪዎችን በምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለጸ

ጥቅምት 1፤2010

የእናት ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት በተያዘው ዓመት ከ22 ሺ በላይ ተማሪዎችን በምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ከዚህ ቀደም የ5ዐ ተማሪዎችን ወጪ በመሸፈን ድጋፍ ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከማህበሩ ጋር የ1 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ድጋፉ የ45ዐ ተማሪዎችን ወጪ የሚሸፍን ሲሆን ድርጅቱ በአጠቃላይ 5ዐዐ ተማሪዎችን በምገባ መርሐ ግብሩ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

የእናት ወግ በጎ አድራጎት ማሕበር የበላይ ጠባቂ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በመርሐ ግብሩ ተጠቃሚ የሆኑት ሕፃናት ለትምህርታቸው ትኩረት በመስጠት ትልቅ መሻሻሎችን ማሳየታቸውን ጠቅሰው ይህን ለማሰቀጠል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ በበኩላቸው ድርጅታቸው በቀጣይ ሕፃናቱን ለመርዳት ከማሕበሩ ጎን ይቆማል ብለዋል፡፡

የእናት ወግ በጎ አድራጎት ማሕበር ሥራ አስኩያጅ ወይዘሮ ደብረወርቅ ልዑለሰገድ እንዳሉት በዘንድሮው አመት የምገባ መርሐ ግብሩን በአዲስ አበባ በሚገኙ 226 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚያካሂድና በቀጣይ በክልሎች ያሉ ሕፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የማሕበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ደብረወርቅ ልዑልሰገድ አስታውቀዋል፡ይሰራል

ዘገባው የሪፖርተራችን ነፃነት ወርቁ ነው፡፡