ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለጉልበት ብዝበዛና ለግዳጅ ጋብቻ ተዳርገዋል:- ተመድ

መስከረም 11፣2010

ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአለማችን ህዝቦች ለዘመናዊ ባርነት እንዲሁም ለግዳጅ የጉልበት ስራና ጋብቻ መዳረጋቸውን የመንግስታቱ ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2016 ያጠናው ጥናት አመልክቷል።

በጥናቱ መሰረት ዋነኞቹ ተጎጅዎች ሴቶችና ልጃገረዶች መሆናቸው ተገልጿል።

ከተጎጅዎች መካከል 25 ሚሊዮን የሚሆኑት ለግዳጅ የጉልበት ስራ እንዲሁም 15 ሚሊዮን የሚሆኑት  የግዳጅ ጋብቻ ተጠቂዎች ናቸው ተብሏል᎓᎓

ከአጠቃላይ ተጎጅዎች 29 ሚሊዮን ወይም 71 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ልጃገረዶች መሆናቸውንም ተመልክቷል᎓᎓

ጥናቱ የተዘጋጀው በአለም አቀፉ የስራ ድርጅት፣ ዎክ ፍሪ ፋውንዴሽንና ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው᎓᎓

በሌላ በኩል የአለም አቀፍ የስራ ድርጅት ለብቻው ስለ ህጻናት የጉልበት ብዝበዛ በአውሮፓውያኑ ከ2012 እስከ 2016 ባስጠናው ጥናት እድሜያቸው ከ5 እስከ 7 የሚሆኑ 152 ሚሊዮን ህጻናት ለጉልበት ብዝበዛ መጋለጣቸው ያሳያል ሲል የዘገበው ሲጂቲኤን ነው᎓᎓