በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመሬት መንኘራተት አደጋ ከ60 በላይ ሰዎች ሞቱ

ነሀሴ 12 ፤2009

በሰሜን ምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የመንሸራተት አደጋ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

የአደጋው መንስኤም በአካባቢው ከባድ ዝናብ በመጣሉ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የኢቱሪ ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ ፓስፊክ ኬታ እንደገለጹት ከሆነ እስካሁን በተገረገው ጥረት አምስት ሰዎችን ህይወት ማትረፍ የተቻለ ሲሆን በርካቶች ደግሞ አልተገኙም፡፡

አብዛኞቹ ሟቾች በአልበርት ሃይቅ ዙሪያ በአሳ ምርት ህይወታቸውን የሚያሰተዳድሩ ነበር ተብሏል፡፡

የተወሰኑት ደግሞ በቀድሞው የወርቅ ማዕድን ማምረቻ ስፍራ ላይ ወርቅ በመፈለግ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

በሀገሪቱ ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንሸራተት አደጋ እንደሚደርስ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፡ አልጀዚራ