ጎግል በሚቀጥሉት ዓመታት 10 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ሊያሰለጥን ነው

ሐምሌ 21፣2009

ጎግል በሚቀጥሉት ዓመታት 10 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በኢንተርኔት ገበያው ግንባር ቀደም የሆነው ጐግል በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በቀጥታ የዘርፉ ክህሎቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና እሰጣለሁ ብሏል፡፡

የጎግል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱንዳር ፒቻይ በናይጀሪያ ሌጎስ  ተገኝተው እንንዳሉት ለ10 ሚሊዮን አፍሪካዊያን የሚሰጠው ስልጠና በኢንተርኔትና ቴክኖሎጂ በገበያ ላይ ተፈላጊ ክህሎት ያቸው ሙያተኞችን ለማፍራት ነው፡፡

ዕድሉን ከሚያገኙት ሰልጣኞች መካከል 40 በመቶዎቹ ሴቶች ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ኩባንያው በናይጄሪያ ፣ኬንያና ደብብ አፍሪካ 100ሺህ ሶፍት ዌር አበልፃጊዎችንም እንደሚያሰለጥን  ይፋ አድርጓል፡፡

ይሁንጂ ጎግል ለስልጠናው ምንያ ያህል በጀት እንደያዘ ያስታወቀው ነገር የለም፡፡

ምንጭ፡‑ ቢቢሲ