ብሪታንያ ለኢትዮጵያ የቤትሰብ ምጣኔ የ90 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ አደረገች

ሐምሌ 5፣2009

ብሪታንያ ለኢትዮጵያ የቤትሰብ ምጣኔ አገልግሎት የሚውል የ90 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ አደረገች፡፡

የብሪታንያ ለአለም አቀፍ የልማት ክፍል እንዳስታወቀው ድጋፉ ለሚቀጥሉት አራት አመታት በፍላጎት ለሚደረግ አዲስ የቤተሰብ ምጣኔ ፕሮግራም የሚውል ነው።

ከኢፌዲሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እንደሚካሄድ የተገለጸው ፕሮግራሙ፣  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶችን የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

በፕሮግራሙ 13 ሚሊዮን ሴቶች ቀጥታ የቤተሰብ እቅድ መረጃ እንዲያገኙ፣አሁን ላይ የቤትሰብ እቅድ እየተጠቀሙ ያሉ 6 ሚሊዮን ሴቶች መደገፍና ተጨማሪ ሶስት ሚሊዮን ፈቃደኛ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማበረታት፣ እንዲሁም 15 ሚሊዮን ያልተፈለገ እርግዝናን እንዲሁም የ3 መቶ ሺህ የእናቶችና ህጻናት ሞትን ማስቀረት ያለመ መሆኑን ከብሪታኒያ መንግስት ድረ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡