በአለም ዙሪያ 65 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ

ሰኔ 12፤2009

በአለም ዙሪያ 65 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን  አስታወቀ፡፡

 ኮሚሽኑ እንደገለፀው በአለም ላይ ከተመዘገው የስደተኞች ቁጥር ከእስካሁኑ ከፍተኛ ሲሆን በሶሪያ በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት ብቻ ከ12 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ከቀዬያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

እነዚህ ስደተኞች በአብዛኛው በስደተኞች  ካምፕ የሚኖሩ፤ ጥገኝነት ፈላጊዎች ወይም የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች  መሆናቸውን  ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

 በ2016 መጨረሻ የተመዘገበው የስደተኞች ቁጥር ከ2015ቱ በ300 ሺ መጨመሩን የኮሚሽኑ አመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

የኮሚሽኑ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ጊራንዲ እንደገለጹት የአለም ፖለቲከኞች ሰላምን ማስፈን አልቻሉም፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ