በፖርቱጋል በተነሳ ሰደድ እሳት የ61 ሰዎች ህይወት አለፈ

ሰኔ 11፤2009

በፖርቱጋል ኮይምብራ ከምትባል ከተማ ደቡብ ምስራቅ በሚገኘው ፔድሮጋዮ ግራንዳ በተባለ አካባቢ በተነሳ ሰደድ እሳት የ61 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እንደባለስልጣናቱ ገለጻ አብዛኞቹ ህይወታቸው ያለፈው ከእሳቱ ለማምለጥ በመኪና እየተጓዙ ሳለ ነው፡፡

በተከሰተው የእሳት አደጋ የነፍስ አድን ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የስምንት ዓመት ህጻን ጨምሮ የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞችም የአደጋው ሰላባ ሆነዋል ተብሏል፡፡

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አንቶንዮ ኮስታ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንዲህ አይነት ከባድ ጉዳት ያስከተለ የደን ቃጠሎ ታይቶ የማይታወቅ ነው ብለዋል፡፡

በአደጋው የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀሰው ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።

የፖርቱጋል የአገር ውስጥ ጉዳይ ፀሓፊ ጆርጅ ጎሜስ እንደሚት ከማቾቹ ውስጥ 30ዎቹ   በመኪናቻው ውስጥ መገኘታቸው ተናግረዋል።

የተነሳውን ሰደድ እሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል 6 መቶ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ