በባህር ዳር በ60 ሚሊዮን ዶላር ያህል የኢንደስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

ሰኔ 2፤2009

62 ሚሊዮን ዶላር በሆነ ወጪ በባህር ዳር ከተማ የኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ ሊካሄድ መሆኑን የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

የፓርኩን ግንባታ ለማስጀመር በቻይናው ሲሲኢሲሲ ኩባኒያ ጋር ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ግንባታው ተጠናቆ በሚዘጋጁት ስምንት ሼዶች ውስጥ የሚገቡት ኩባኒያዎች የሀገሪቱን የኢንደስትሪ አቅጣጫ የተከተሉ ናቸው ተብሏል፡፡

በፓርኩ ግንባታ ሂደትም በርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጠርላቸው ተነግሯል፡፡

ስምምነቱን የፈረመው የቻይናው ኩባኒያ ግንባታውን በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ተስማምቷል፡፡

በባህር ዳር የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢን የማይበክልና መሰረተ ልማት ከወዲሁ የሚሟሉለት እንደሆነ ነስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡