ማርክ ዙክበርግ ፌስ ቡክን ለማስጀመር ብሎ ያቋረጠውን ትምህርት ከ12 አመት በኋላ አጠናቀቀ

ግንቦት 18፤2009

ማርክ ዙክበርግ ፌስ ቡክን ለመጀመር ብሎ  ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ  ያቋረጠውን ድግሪውን ከ12 አመት በኋላ አጠናቆ ተመረቀ᎓᎓

ዙክበርግ ፌስቡክን እውን ያደረገው ኮምፒውተር ሳይንስ በሚያጠናበት ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ  በማደሪያ ክፍሉ ውስጥ ሆኖ እ.ኤ.አ በ2004 ነው ᎓᎓

የፌስ ቡክ መስራች ማርክ ዙክበርግ ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ከቋረጡ ስመ ጥር  ሰዎች ዋነኛው ነው᎓᎓

በዚህ ሳምንት ግን ወደ ሀርቫርድ ኢቪይ ሊግ ትምህርት ቤት በመመለስ ለ12 አመት ያቋረጠውን ትምህርቱን በማጠናቀቅ  ለክብሩ ሲል ዲግሪውን ወስዷል᎓᎓

ሚስተር ዙክበርግ ከአለማችን ሃብታም ሰዎች አንዱ ነው᎓᎓በዚህ አመት ለተመራቂ ተማሪዎች በአመቱ የትምህርት መክፈቻ ላይ ተገኝቶ  "እኔ ያላሳካሁትን እናንተ ግን አሳካችሁት" በማለት ቀስቃሽ ንግግር አድርጓል᎓᎓

ማርክ  ዙክበርግ ፌስቡክን በ2004 እውን ሲያደርግ፣ የማህበራዊ  ትስስር አገልግሎት እንዲሰጥ መጀመሪያ ላይ ለሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ብቻ ነበር የሞከረው᎓᎓

ከዚህ ሳምንት ቀደም ብሎ ፎርብስ መፅሄት ፌስቡክን ከአለማችን  በጣም ውድ ዋጋ ከሚያወጡ ተቋማት  በአራተኛ ደረጃ አስቀምጦታል፡፡

ዙክበርግ በአሁኑ ጊዜ ከአለማችን 5ኛው ሃብታም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ምንጭ ፡ኢንዲፔንደንት