በሻሸመኔና በዶዶላ በ60 ሚሊዮን ብር የተገነቡ የዱቄት ፋብሪካዎች ተመረቁ

ግንቦት 11፣2009

በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔና ዶዶላ በ60 ሚሊዮን የተገነቡ የዱቄት ፋብሪካዎች ተመርቀዋል።

በሻሸመኔ ኡታዋዩ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ማሕበር በ28 ሚሊዮን ብር የተገነባው የዱቄት ፋብሪካ አሁን ላይ ወደ ግብርና ማቀነባበሪያ እየገባ ነው። 

ፋብሪካው በምዕራብ አርሲ ዞን ለሚገኙ ሰባት ወረዳ አርሶ አደሮች የግብርና ግብአትን ያቀርባል ተብሏል።

በተመሳሳይ በ32 ሚሊዮን ብር በዶዶላ የተገነባው የራያ ዋከና ሁለገብ የሕብረት ስራ ማህበር የዱቄት ፋብሪካም ዛሬ ተመርቋል።

በምርቃ ስነ-ስርአቱ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሀለፊዎች ተገኝተዋል።

ስራ ማሕበሩ በሰላሳ ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የፓስታና ሞኮረኒ ማምረቻ የምግብ ኮምፕሌክስም በአቶ ለማ መገርሳ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትር ዶክተር እያሱ አብርሀ የገበሬዎች የስራ ማሕበራት የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬን በማዳን አስተወጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሪፖርተር :-ብሩክ ተስፋዬ